ውክፔዲያ - ዴቪድ ሁም ዴቪድ ሁም ከውክፔዲያ Jump to navigation Jump to search ዴቪድ ሁም ዴቪድ ሁም (ግንቦት 7 1711 - ነሐሴ 25 1776) የነበረ የስኮትላንድ ታሪከኛ እና ፈላስፋ ነበር። [1] ሁም በዘመኑ ይታወቅ የነበረው በታሪክ ተመራማሪነት ነበር። የእንግሊዝ ታሪክ የሚሉ ትላልቅ መጻሕፍትን በዘመኑ ደርሶ ለህትመት አብቅቶ ነበር። አሁን ግን ሁም የሚታወቀው በዋና ፈላስፋነቱ ነው። በፍልስፍና መጽሕፉ ላይ እንደሚያስረዳ ብዙው የሰው ልጅ አምኖ የሚቀበላቸው ነገሮች በ በምክንያት የተደገፉ አይደሉም። ይልቁኑ ከስሜትና ደመነፍስ የሚመነጩ ናቸው። ለምሳሌ አምክንዮ የአንድ ነገር መንስኤ ሌላ ነገር ነው ብሎ አይናገርም። ነገር ግን አንድ ክስተት ሲፈጠርና ከዚያ ቀጥሎ ሌላ ክስተት ሲፈጠር ስናይ የመጀመሪያው ክስተት ለሚቀጥለው ክስተት መንስኤ ነው ብለን በ"ስሜት" እንደመድማለን። በተመሳሳይ አንድ ሰው ሰናይ ግለሰብ እንደሆነ ምክንያት አይነግረንም። ይልቁኑ ያ ሰው ደግና ተግባቢ ሆኖ ስናየው በስሜት ሰናይ ነው እንላለን። እኒህ ነገሮች ከምክንያት አይመነጩም ብሎ ሁም ስለሚያምን ተጠራጣሪ ወይንም ኢ-ምክንዮት ፈላስፋ ተብሎ ይታወቃል። ሁም ሃይማኖት ላይም ተጠራጣሪ ነበር[1]። ሁም ሃይማኖተኛ ሰው አልነበረም። በተአምራትም አያምንም ነበር። የሁም ሐውልት፣ ኤደንብራ፣ ስኮትላንድ የሁም ዋና ዋና መጻሕፍት[ለማስተካከል | ኮድ አርም] A Treatise of Human Nature: Being an Attempt to introduce the experimental Method of Reasoning into Moral Subjects.[1] (1739-40) በዚህ መጽሐፍ፣ ሁም ስለ ሰው ልጅ አዕምሮ በመተንተን እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት ይሞክራል። ስለ ሰው ልጅ እውቀት፣ ስለ መንስኤና ውጤት፣ ስለ የሰው ልጅ ስሜትምና ስለ ደግና ክፉ ይፈላስፋል። An Enquiry Concerning Human Understanding (1748) በዚህች ትንሽ መጽሓፍ ውስጥ ከላይ የቀረበውን መጽሐፍ ሃሳቦች በማሳጠርና ለማንበብ እንዲመቹ በማድረግ ተንትኗል። An Enquiry Concerning the Principles of Morals (1751) ትንሽና ለማንበብ ምቹ የሆነች መጽሐፍ ስትሆን የመጽሐፉ ትኩረት ስለ ደግና ክፉ ይተነትናል Dialogues Concerning Natural Religion[1] (after Hume died) በዚህ መጽሐፉ 3 ገጸ ባህርያት ስለ አምላክ ሲከራከሩ ይነበባል ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም] ^ ሀ ለ ሐ መ Gay, Peter; Time-Life Books (1966). "In Search Of An Ideal Society". Age of Enlightenment. Time. pp. 53.  ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=ዴቪድ_ሁም&oldid=323407» የተወሰደ መደቦች: የስኮትላንድ ሰዎች ፈላስፋዎች Navigation menu የኔ መሣርያዎች አልገቡም ውይይት ለዚሁ ቁ. አድራሻ Contributions የብዕር ስም ለማውጣት ለመግባት ክፍለ-ዊኪዎች መጣጥፍ ውይይት Variants ዕይታዎች ለማንበብ አርም ማዘጋጀት ታሪኩን አሳይ More ፍለጋ የማውጫ ቁልፎች ዋና ገጽ የተመደበ ማውጫ በቅርብ ጊዜ የተለወጡ ማናቸውንም ለማየት እርዳታ ምንጭጌ ወቅታዊ ጉዳዮች (ዜና) መዋጮ ለመስጠት ጠቃሚ መሣሪያዎች ወዲህ የሚያያዝ የተዛመዱ ለውጦች ልዩ ገጾች የዕትሙ ቋሚ URL የዚህ ገጽ መረጃ መጥቀሻ ለዚህ መጣጥፍ የውሂብ ንጥል ነገር Print/export Create a book Download as PDF ለማተሚያዎ እንዲስማማ In other projects Wikimedia Commons በሌሎች ቋንቋዎች Afrikaans Aragonés العربية مصرى Asturianu Azərbaycanca Беларуская Беларуская (тарашкевіца)‎ Български বাংলা Brezhoneg Bosanski Català کوردی Čeština Cymraeg Dansk Deutsch Ελληνικά English Esperanto Español Eesti Euskara Estremeñu فارسی Suomi Français Nordfriisk Frysk Gaeilge Gàidhlig Galego עברית हिन्दी Hrvatski Magyar Հայերեն Bahasa Indonesia Ido Íslenska Italiano 日本語 ქართული Қазақша ಕನ್ನಡ 한국어 Kurdî Кыргызча Latina Lëtzebuergesch Lingua Franca Nova Lumbaart Lietuvių Latviešu Malagasy Македонски മലയാളം Монгол Bahasa Melayu Plattdüütsch Nederlands Norsk nynorsk Norsk bokmål Occitan Livvinkarjala ਪੰਜਾਬੀ Polski Piemontèis پنجابی Português Runa Simi Română Русский Sicilianu Scots Srpskohrvatski / српскохрватски Simple English Slovenčina Slovenščina Shqip Српски / srpski Svenska Kiswahili தமிழ் ไทย Tagalog Türkçe Татарча/tatarça Українська Oʻzbekcha/ўзбекча Tiếng Việt Volapük Winaray 吴语 ייִדיש Yorùbá 中文 Bân-lâm-gú 粵語 Edit links ይህ ገጽ መጨረሻ የተቀየረው እ.ኣ.አ በ16:36፣ 25 ማርች 2015 ዓ.ም. ነበር። የዚህ መዝገበ ዕውቀት ጽሁፍ በክሪኤቲቭ ኮመንስ ፈቃድ (Creative Commons Attribution/Share-Alike License) ስር ነው የተለቀቀው፣ ተጨማሪ ደንቦች ሊኖሩ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ የአጠቃቀም ደንቦችን ይዩ። የግልነት ድንጋጌ ስለ ውክፐድያ መርሃግብር የኃላፊነት ማስታወቂያ የሞባይል ዕይታ ለገንቢዎች Statistics Cookie statement