ውክፔዲያ - አማኑኤል ካንት አማኑኤል ካንት ከውክፔዲያ Jump to navigation Jump to search ኢማኑኤል ካንት (1724 - 1804) አማኑኤል ካንት ( Immanuel Kant) ከ(1724-1804) የነበረ ጀርመናዊ ፈላስፋ ሲሆን በምስራቃዊ ፕሩሲያ፣ ኮይንበርግ ከተማ ተወልዶ፣ ከዕለተ ውልደቱ እስከ እለት ሞቱ ከኮይንበርግ 50 ማልይ በላይ ሳይሄድ በዛች በትወሰነች ከተማ ኑሮውን መርቷል። ካንት በርግጥ ውጫዊ ህይወቱ ብዙ ለውጥ ያልታየበት ቢሆንም፣ በአስትሳሰብ ግን የዘመኑን ፍልስፍና ከስር-መሰረቱ ቀይሯል። "ቀኝ" እና "ግራ" በኅዋ ውስጥ እንዴት ሊለዩ ይችላሉ የሚለውን ጽሁፍ በ1770 ለዶክትሬቱ መመረቂያ ካቀረበ ጀምሮ ለዘመናዊ ፍልስፍና ያለመታከት ብዙ ጽሁፎችን አቅርቧል። በነዚህ ጽሁፎች ውስጥ የካንት መሪ ሃሳብ "ማንኛውም የሰው ልጅ እውቀት ከበስተጀርባው የሰው ልጅን አእምሮ በተነሳሽ (active) ተሳታፊነት ያጠይቃል" የሚል ሲሆን፣ በርግጥ ይህ አስተሳሰብ ቀላል መስሎ ቢታይም ውስጡ ግን ብዙ ከባድና የተወሳሰቡ ጽንሰ ሃሳቦችን በመያዙ ከሱ በኋላ ለተነሱ ፈላስፋወች የሃሳብ ውቅያኖስ በመሆን እስካሁን ዘመን ድረስ በሱ ስራ ላይ ጥናት ይካሄዳል። ማውጫ 1 ትችት በአምክንዮ ላይ 2 ግብረ ገብ 3 በቀሪው ዘመኑ 4 ማጣቀሻወች ትችት በአምክንዮ ላይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም] በ1781 እና በ1787 ባሳተመው የንጹህ አምክንዮ ትችት (ጀርመንኛ፡ Kritik der reinen Vernunft) መጽሃፉ ላይ፣ የሂሳብ፣ ሳይንስ እና ስነ ውን እውነታወችን ለመገንዘብ የሚያስፈልጉን ቅድመ ነገሮች ምንድን ናቸው? የሚለውን ጥያቄ ባማንሳት የተሟላ መልስ ለመስጠት ሞክሯል። ካንት የሰውን ልጅ ግንዛቤ በሁለት ከፍሏል፣ እነሱም ቀዳሚ (ማለት ከተሞክሮ ውጭ የሚታወቅ እውነት (a priori or analytic)) እና ተከታይ(ፍልስፍና) (ማለት ከተሞክሮ በኋላ የሚገኝ እውቀት (a posteriori)) ናቸው። ነገር ግን ካንት ከሁሉ ሁሉ ትኩርት የሚስቡና በርግጥም በጣም ጠቃሚ ዕውቀት ናቸው ያላቸው ተከታይ(ፍልስፍና) ቀዳማዊ ግንዛቤ ናቸው ያላቸውን ነው። እነዚህም እውነታወችን ለመገንዝብ በርግጥ የሰው አዕምሮ በምን አይነት ሁኔት እንዳለ እራሱን ማወቅ ይኖርበታል ይላል ካንት። ከዚህ በመነሳት በሂሳብም ሆነ በሳይንስም ሆነ በለት ተለት ህይወታችን ውስጥ ቁስ አካሎች በኅዋ እና ጊዜ ውስጥ ተንጣለው እንድሆኑ አድርገን የምንገነዘብበት ምክንያት አእምሯችን እራሱ ጊዜንና ኅዋን በማፍለቅ ቁስ አካላትን በዚህ እራሱ ባፈለቀው ሁለት ጽንሰ ሃሳቦች ስለሚደረድራቸው ነው ይላል። በሳይንስም በኩል ማናቸውንም ተመክሮ በ መንስዔ እና ክትለት (cause and effect) ሰንሰለት አያይዞ የሚያስገነዝበን አዕምሯችን ነው። ግን እነዚህ አይነት መሪ ሃሳቦች የሚሰሩት ለምናውቀው የተሞክሮው አለም እንጂ ሥነ መልኮት እና ሥነ ውን (metaphysics) በሚያጠኑት ከተሞክሮ ውጭ ለሆነው ለሌላው አለም አይሰራም። ግብረ ገብ[ለማስተካከል | ኮድ አርም] <<ካንት>> ከዚህ በተጨማሪ የግብረ ገብ ፈላስፋ ነበረ። ስለሆነም በ1785 (ጀርመን፡ Grundlegung zur Metaphysik der Sitten) የግብረገብ መሰረት ሥነ ውን የሚለውን መጽሃፉን ለህትመት አቅርቧል። .በዚህ ትንተናው ለሁሉም የሰው ልጅ የሚሰራ ብሎ ያመነበትን ዓለም አቀፍ ግብረገብ አበርክቷል። እኒህን የግብረገብ ህጎች የሁልጊዜ ግዴታ በማለት ተንትኗል። ይህ የሁልጊዜ ግዴታ ሲብራራ እንዲህ ይላል፡ አንድ ነገር ስትፈጽም (ስታደርግ) ያ ያደረከው ስራ ዓለም አቀፋዊ ህግ እንዲሆን በመፍቀድ ይሁን [1]ይላል። ለምሳሌ፡ ዛሬ ብትሰርቅ፣ መስረቅ ላንድ ጊዜ ብቻ የተፈቀደ ሳይሆን ለሁሉል ብሁሉም እንዲፈቀድ ፈቃድህ ይሁን፣ አለበለዚያ አትስረቅ ማለት ነው። ወይም ደግሞ እውነት ለመናገር ከወሰንክ፣ ላንድ ጊዜ ብቻና ላንተ ብቻ ሳይሆን ለሁሉ ሰው በሁሉ ቦታ እውነት እንዲናገሩ ፈቃድህ ነው ማለት ነው። በሌላ ቋንቋ፣ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለሁሉ ሰው፣ በሁሉ ጊዜ ፣ በሁሉ ቦታ እንዲደረግ የምትፈቅደውን ነገር ብቻ አድርግ። ካንተ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የእግዚአብሄርን መኖር፣ የነጻነትን መኖር፣ እና ዘላለማዊ ኑሮን እንደመነሻ በመውሰድ ነበር። በቀሪው ዘመኑ[ለማስተካከል | ኮድ አርም] በቀሪው ዘመኑ፣ <<ካንት>>፣ ሳይንስና አርትን በማዋሃድ በአንድ አይን ሊመለከታቸው በቃ። (ጀርመን፡ Kritik der Urteilskraft (Critique of Judgment) (1790). ከዚያም ስለ ሃይማንቶ በ1793 ጽሁፍ አቅርቧል (ጀርመን፡ Die Religion innerhalb die Grenzen der blossen Vernunft (Religion within the Limits of Reason Alone))። ቀጥሎም <<መማር>> ማለት ምን ማለት ነው ለሚውለው ጥያቄ (ጀርመን፡ Beantwortung der Frage: Was ist Aufklärung? ("What is Enlightenment?" (1784)) መልስ ሲስጥ በስተመጨረሻ በ1795 አለም አቀፍ ትብብር በሁሉ አለም እንዲኖር ተማጽኗል (ጀርመን፡ in Zum ewigen Frieden (Perpetual Peace) )። ማጣቀሻወች[ለማስተካከል | ኮድ አርም] ^ Kant, Immanuel; translated by James W. Ellington [1785] (1993). Grounding for the Metaphysics of Morals 3rd ed.. Hackett. pp. 30. ISBN 0-87220-166-x.  ከ «https://am.wikipedia.org/w/index.php?title=አማኑኤል_ካንት&oldid=323232» የተወሰደ መደቦች: ፈላስፋዎች የጀርመን ሰዎች Navigation menu የኔ መሣርያዎች አልገቡም ውይይት ለዚሁ ቁ. አድራሻ Contributions የብዕር ስም ለማውጣት ለመግባት ክፍለ-ዊኪዎች መጣጥፍ ውይይት Variants ዕይታዎች ለማንበብ አርም ማዘጋጀት ታሪኩን አሳይ More ፍለጋ የማውጫ ቁልፎች ዋና ገጽ የተመደበ ማውጫ በቅርብ ጊዜ የተለወጡ ማናቸውንም ለማየት እርዳታ ምንጭጌ ወቅታዊ ጉዳዮች (ዜና) መዋጮ ለመስጠት ጠቃሚ መሣሪያዎች ወዲህ የሚያያዝ የተዛመዱ ለውጦች ልዩ ገጾች የዕትሙ ቋሚ URL የዚህ ገጽ መረጃ መጥቀሻ ለዚህ መጣጥፍ የውሂብ ንጥል ነገር Print/export Create a book Download as PDF ለማተሚያዎ እንዲስማማ In other projects Wikimedia Commons በሌሎች ቋንቋዎች Afrikaans Alemannisch Aragonés العربية الدارجة مصرى Asturianu Aymar aru Azərbaycanca تۆرکجه Башҡортса Žemaitėška Bikol Central Беларуская Беларуская (тарашкевіца)‎ Български भोजपुरी বাংলা Brezhoneg Bosanski Буряад Català Chavacano de Zamboanga Нохчийн Cebuano کوردی Čeština Чӑвашла Cymraeg Dansk Deutsch Zazaki Ελληνικά Emiliàn e rumagnòl English Esperanto Español Eesti Euskara Estremeñu فارسی Suomi Võro Føroyskt Français Arpetan Nordfriisk Frysk Gaeilge 贛語 Kriyòl gwiyannen Gàidhlig Galego ગુજરાતી עברית हिन्दी Fiji Hindi Hrvatski Magyar Հայերեն Interlingua Bahasa Indonesia Interlingue Ilokano Ido Íslenska Italiano 日本語 Patois Jawa ქართული Qaraqalpaqsha Taqbaylit Kabɩyɛ Қазақша ಕನ್ನಡ 한국어 Kurdî Кыргызча Latina Lëtzebuergesch Лезги Lingua Franca Nova Limburgs Ligure Ladin Lumbaart لۊری شومالی Lietuvių Latviešu मैथिली Malagasy Македонски മലയാളം Монгол मराठी Кырык мары Bahasa Melayu Malti Mirandés မြန်မာဘာသာ Эрзянь Nāhuatl Plattdüütsch नेपाली नेपाल भाषा Nederlands Norsk nynorsk Norsk bokmål Occitan Livvinkarjala ਪੰਜਾਬੀ Polski Piemontèis پنجابی پښتو Português Runa Simi Rumantsch Română Русский Русиньскый Kinyarwanda संस्कृतम् Саха тыла Sardu Sicilianu Scots Srpskohrvatski / српскохрватски Simple English Slovenčina Slovenščina Shqip Српски / srpski Sunda Svenska Kiswahili தமிழ் తెలుగు Тоҷикӣ ไทย Tagalog Tok Pisin Türkçe Татарча/tatarça Українська اردو Oʻzbekcha/ўзбекча Vepsän kel’ Tiếng Việt West-Vlams Volapük Winaray 吴语 მარგალური ייִדיש Yorùbá Zeêuws 中文 文言 Bân-lâm-gú 粵語 Edit links ይህ ገጽ መጨረሻ የተቀየረው እ.ኣ.አ በ16:07፣ 25 ማርች 2015 ዓ.ም. ነበር። የዚህ መዝገበ ዕውቀት ጽሁፍ በክሪኤቲቭ ኮመንስ ፈቃድ (Creative Commons Attribution/Share-Alike License) ስር ነው የተለቀቀው፣ ተጨማሪ ደንቦች ሊኖሩ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ የአጠቃቀም ደንቦችን ይዩ። የግልነት ድንጋጌ ስለ ውክፐድያ መርሃግብር የኃላፊነት ማስታወቂያ የሞባይል ዕይታ ለገንቢዎች Statistics Cookie statement